የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ላይ የኢሌክትሪክ ሃይል መቆራረጥን ለማስቀረት ስምምነት ተፈረመ

የኢትዮጵያ ጅቡቲ ምድር ባቡር እና የኢትዮጵያ ኢሌክትሪክ ሃይል በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱ በባቡር መስመሩ ላይ የሚታየውን የኤሌክትሪክ ሃይል መቆራረጥ ችግር በዋነኝነት ለመቀርፍ የሚያስችል ነው ተብሏል። ስምምነቱን የኢትዮጵያ ጅቡቲ ምድር ባቡር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አብዲ ዘነበ እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ስራ አስኪያጅ አቶ አሸብር ባልቻ ተፈራርመዋል። በሁለቱ ተቋማት የተደረገው ስምምነት ጠንካራ ግኑኝነት በመፍጠር ችግሮቹን በዘላቂነት ለመፍታት ያለመ ሲሆን፥ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት በአጭር፣ በመካከለኛ እና በረጅም ጊዜ የሚፈቱ ጉዳዮች መለየታቸው ተገልጿል። ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ ጅቡቲ ምድር ባቡር ዋና ስራ ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አብዲ ዘነበ የተደረገው ስምምነት በባቡር መስመሩ ላይ የሚታየውን የሃይል መቆራረጥ ችግር የሚያስቀር ነው ብለዋል ።
እንዲሁም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ስራ አስኪያጅ አቶ አሸብር ባልቻ በበኩላቸው ተቋማቱ ያላቸውን ግኑኝነት ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ እና ያላቸውን ሃብቶች በጋራ ለመጠቀም የሚያስችል ነው ብለዋል። የሁለቱ ተቋማት በጋራ ተቀናጅቶ መስራት ለተቋማቱም ሆነ ለሃገርቱ ከፍተኛ ጥቅም እንዳለውም ተነግሯል ።